የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከፍተኛ አመራሮች በአፋር እና አማራ ክልል ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች እና አካባቢዎች ጎብኙ


8/23/2021 8:18:39 AM
ፒዲኤፍ ዳውንሎድ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከፍተኛ አመራሮች በአፋር እና አማራ ክልል ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች እና አካባቢዎች ጎብኙ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከፍተኛ አመራሮች በሦስት ቡድን በመከፈል በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሕወሃት በፈጸመው ጥቃት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን እና በአካባቢው ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ ለመጎብኘት ያደረጉትን ጉዞ አጠቃለው እየተመለሱ ነው። በአፋር እና በደሴ በኩል ጉብኝት ያደረጉት አመራሮች ጉብኝታችን ጨርሰው ወደ አዲስ አበባ የተመለሱ ሲሆን በጎንደር በኩል ጉብኝት እያደረገ የሚገኘው የአመራር ቡድን ነገ ማክሰኞ ነሐሴ 18 ጉብኝቱን አጠናቆ እንደሚመለስ ታውቋል። በአፋር ክልል በኩል ጉብኝት ያደረጉት አመራሮች ሰመራ ከተማ በመገኘት ከክልሉ አደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት እንዲሁም ከክልሉ ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር በክልሉ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን ወደጭፍራ በማምራት ሕወሃት በፈፀመው ጥቃት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የሚገኙበትን ሁለት ጊዚያዊ መጠለያ ጣቢያዎችን ጎብኝተው ያለውን ሁኔታ ለመረዳት ችለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በጭፍራ ከሚገኙ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።....[ ሙሉውን ለማንበብ የተያያዘውን PDF ፋይል ያውርዱ]