ዋና ገጽ
አወቃቀራችን
ከፍተኛ አመራሮች
ኢዜማን ለምን ይመርጣሉ?
ዐቢይ መልዕክቶች
ስራ አስፈጻሚ
ዕጩዎች
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በሕወሃት መራሹ ኃይል ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ እና ቤተሰቦቻቸውን ላጡ በሰሜን ጎንደር ጭና ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።
9/24/2021 2:52:13 AM
ፒዲኤፍ ዳውንሎድ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በሕወሃት መራሹ ኃይል ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ እና ቤተሰቦቻቸውን ላጡ በሰሜን ጎንደር ጭና ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አደረገ። ድጋፉን ለማድረስ በጭና የተገኙት የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ኑሪ ሙደሲር ኢዜማ ከአራት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጉን በመግለጽ «የሕዝባችን ችግር የእኛም ችግር ነው ብለን ነው እዚህ የተገኘነው» ብለዋል። «በዚህ ወቅት በተለያየ ጎራ የምንሰለፍበትም ጊዜ አይደለም። በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በብሔር ምክንያት ተለያይተን የምንቆምበት ጊዜ ሳይኾን ሀገራችንን የመጣባትን ጠላት ተከላክለን ኢትዮጵያ ለሚቀጥለው ትውልድ የምናስረክብበት ጊዜ ነው። ጦርነት ጥሩ ነው ባይባልም ሕወሓት በፈጠረብን ችግር ሕዝቡ ወደ አንድ ጎራ እየተሰለፈ ነው። ከዚህ በፊት ሕወሃት በታትኖን የነበረ ቢሆንም አሁን ወደ አንድ መስመር ተሰልፈን ሀገራችንን ለማገልገል ተነስተናል።» ሲሉ ድጋፉ ከተደረገ በኋላ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል። [ሙሉውን ለማንበብ የተያዘዘውን PDF ያውርዱ]