ዋና ገጽ
አወቃቀራችን
ከፍተኛ አመራሮች
ኢዜማን ለምን ይመርጣሉ?
ዐቢይ መልዕክቶች
ስራ አስፈጻሚ
ዕጩዎች
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ የአቋም መግለጫ
10/3/2021 6:29:43 AM
ፒዲኤፍ ዳውንሎድ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ጉባዔውን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከሚገኙ የምርጫ ወረዳዎች የተወከሉ የፓርቲው አባላት በተገኙበት መስከረም 22 እና 23 ቀን 2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ ጉባዔው በተለያዩ ሀገራዊ እና ድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ሲወያይ ቆይቶ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡ 1. ፓርቲው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ምርጫ 2013 በተካሄደ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ የደንብ ማሻሻያ እንዲያደርግ በመጠየቁ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቶ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲሻሻሉ የተሰጡ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀፆች እና ባለፉት አመታት ሊያሰሩ አልቻሉም የተባሉ የተለያዩ የመተዳደሪያ ደንቡ አንቀፆችና ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ላይ የቀረበውን ማሻሻያ በ595 ድጋፍ፣ 3 ተቃውሞ እና 32 ድምጸ ተዓቅቦ አፅድቆ የተሻሻለው ደንብ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲገባ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ [ሙሉውን ለማንበብ የተያያዘውን PDF ያውርዱ።]