ዋና ገጽ
አወቃቀራችን
ከፍተኛ አመራሮች
ኢዜማን ለምን ይመርጣሉ?
ዐቢይ መልዕክቶች
ስራ አስፈጻሚ
ዕጩዎች
ኢዜማ፣ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ዘክሮ ዋለ
3/8/2022 7:17:19 AM
ፒዲኤፍ ዳውንሎድ
ኢዜማ፣ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ዘክሮ ዋለ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሴቶች ጉዳይ መምሪያ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8ትን "ሴቶች ለሰላም እና ለፍትህ" በሚል መሪ ቃል አከበረ። ዕለቱን በማስመልከት የመነሻ ፅሁፋ ያቀረቡት የኢዜማ ሴቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ለይላ አሊ፣ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዴት መከበር እንደጀመረ ገለፃ አድርገዋል። እ.ኤ.አ በ1910 በዴንማርክ ዋና ከተማ ኮፐን ሀገን በተካሄደ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ ላይ 100 የሚሆኑ የኮንፍረንሱ ተሳታፊ ሴቶች፣ ሃሳባቸውን ካቀረቡ በኋላ 17 ሀገራት ጥያቄውን ስለተቀበሉት እ.ኤ.አ ከ1911 ጀምሮ ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተብሎ መከበር እንደጀመረ ኃላፊዋ አስረድተዋል። በኢትዮጵያም ለ46ኛ ጊዜ እየተከበረ እንዳለ ገልፀዋል። ሴቶችና ህፃናት ባለፉት ሁለት ዓመት ይህ ነው የማይባል ግፍ እና በደል ሲደርስባቸው እንደነበር የገለፁት የሴቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊዋ ለይላ አሊ፣ ዛሬ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ማስቆም ካልተቻለ ነገ የጥቃቱ ሰለባ ያልሆኑ ሴቶች የጥቃቱ ሰለባ የማይሆኑበት ምክንያት እንደሌለ ጠቁመዋል። ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆምም ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ድርጊቱን ማውገዝ እንደሚገባው ተናግረዋል። የስርዓተ-ፆታ እኩልነት አሁን! #ሴቶች_ለማኅበራዊ_ፍትህ #ኢዜማ #ኢትዮጵያ