የውጪ አገራት ባንኮች በኢትዮጵያ…?” በሚል ርዕስ የተካሄደው ፓናል ውይይት ገንቢ ሀሣቦች የተገኙበት ሆኖ ተጠናቋል!


3/21/2022 3:14:47 AM
ፒዲኤፍ ዳውንሎድ

የውጪ አገራት ባንኮች በኢትዮጵያ…?” በሚል ርዕስ የተካሄደው ፓናል ውይይት ገንቢ ሀሣቦች የተገኙበት ሆኖ ተጠናቋል! የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት የውጪ ባንኮች ወደ አገር ውስጥ መግባት ያለውን አዎንታዊና አሉታዊ ጎኖች ያሳየ ነበር፡፡ በመድረኩ አቶ ያሬድ ኃይለመስቀል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተጋረጠበትን አደጋ አስረድተው መውጫ መንገድ ያሏቸውን ዳሰዋል፡፡ “እውነተኛ ውድድር ወዳጅ የላትም” በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት አቶ ኢየሱስወርቅ ዛፉ ባለፉት 30 ዓመታት ባንኮቻችን የሄዱበትን መንገድ በማሳየት የዉጪ ባንኮች መግባት ለዘርፉ ዕድል ሊሆን ይችላል ነገር ግን አገባባቸው በዕቅድ፣ በሒደትና በደረጃ ሊሆን እንደሚገባ አስቀምጠዋል፡፡ የፓናል ውይይቱን በማስኬድ መድረኩን የመሩት አቶ ግርማ ሰይፉ በበኩላቸው የፋይናንስ ዘርፍ ለአገር የሚያበረክተው ሚናን አስምረው የፋይናንስ ተቋማቱ ገንቢ ሚና በሚወጡበት መልኩ ቁመናቸውን መገንባት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ ከፓናሊሰቶቹ የተነሱ ጠቃሚና ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦችን በመውሰድ ኢዜማ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ እንደሚያቀርብ የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ ጸሃፊ አቶ ይመስገን መሳፍንት አሳውቀዋል፡፡ #ኢዜማ #ኢትዮጵያ