ኢዜማ በአስሩ ክልሎችና በሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች ላይ ምርጫ ወረዳን መሰረት ባደረገ አደረጃጀት እስከ ነሐሴ ወር 2012 ድረስ በመላው ኢትዮጵያ በ45 ዞኖች ውስጥ ባሉ 435 የምርጫ ወረዳዎች ላይ መዋቅሩ የተዘረጋ ሲሆን በአጠቃላይ 278 የምርጫ ወረዳ ቢሮዎች ሊኖሩት ችሏል፡፡ ኢዜማ ከመተማ እስከ ጉባ፣ ከጉግ እስከ ቤና ፀማይ ፣ ከጅግጅጋ እስከ አዶላ ኢትዮጵውያን ባሉበት ሁሉ የሚገኝ ፓርቲ ነው፡፡
ፖለቲካ ማኅበረሰባችንን በጋራ የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ የሚሰጥበት ስለሆነ የሁላችንም የጋራ መገለጫ የሆነው ዜግነትን መሰረት ያደረገ ፖለቲካ ላይ መመስረቱ እና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ፅኑ አቋም ያለው በመሆኑ
የማኅበራዊ ፍትህ ፍልስፍናን መሰረት በማድረግ እያንዳንዱ ዜጋ በሃገራችን ያሉትን ዕድሎች በእኩል ደረጃ ያለመድልዎ የሚጠቀምበትን ሥርዓት መፈጠር እንዳለበት የሚያምን በመሆኑ
እውቀትን መሰረት ያደረገ በሃገራችን ላሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጡ የሚችሉ የፖሊሲ አማራጮች በማዘጋጀቱ እና እውነተኛ ፌዴራላዊ ስርዓት በመገንባት ዜጎች ከአከባቢያቸው ጀምሮ በመረጡትን ተጠያቂነቱ ለሕዝብ በሆነ አስተዳደር እንዲመሩ በማድረግ ሥልጣንን ለእውነተኛ ባለቤቱ ህዝብ ቅርብ እንዲሆን ስለሚሰራ
ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ
ወረዳዎች ላይ
ወጣት የብሄራዊ ስራ አስፈጻሚ አባላት
ሴት የብሄራዊ ስራ አስፈጻሚ አባላት